ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ አውደ ርዕይ ላይ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እያስተዋወቀች ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ አውደ ርዕይ ላይ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች።

ከትናንት በስቲያ በተጀመረው አውደ ርዕይ ላይ ከ909 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአውደ ርዕዩ ላይ የኢትዮጵያን ቱሪስት መዳረሻዎች እና የቡና ሀብት ለጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።


 

ኤምባሲው ከሩሲያ ዋና ዋና አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ከ16 ሺህ በላይ ጎብኚዎች አውደ ርዕዩን እንደሚጎበኙት ይጠበቃል።

31ኛው የዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ አውደ ርዕይ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ኢዜአ በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም