የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:- - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ቢሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛል፡፡
ከቀረቡት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከልም፡-
ዘላቂ የሰላም ግንባታን በማጠናከር የሀገሪቱን የልማት ፤የዴሞክራሲ እና አንድነት ከማስቀጠል አንጻር መንግስት ምን እቅድ ይዟል?
ታላቁ የህዳሴ ግድብ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች የመብራት አገልግሎት የሚያገኘኙት ከሌላ ቦታ በመሆኑ የመብራት መቆራረጥ በስፋት ይታያል።አካባቢዎቹ መብራት ቀጥታ ከህዳሴ ግድቡ የሚያገኙበት ሁኔታ ቢመቻች፥
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች መንገድን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ምን እየተሰራ ነው?
መንግስት ለምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ ለማስገባት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የአፈጻጸም ደረጃ ምን ደረጃ ላይ ደርሷል?
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም እና ህዝባዊ ተሳትፎ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
መንግስት መንገድ እና ኤሌክትሪክ ሃይልን ጨምሮ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መሰረተ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ ምን እየሰራ ነው? የሚሉት ይገኙበታል።