ቀጥታ፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-

 

👉የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ለመመለስ መንግስት እያካሄደ የሚገኘው የዲፕሎማሲ ስራ እጅግ የሚበረታታ ነው፥

👉በኢትዮጵያ ከከተማ እስከ ገጠር እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያን ገጽታ የሚቀይር ነው፥

👉በትግራይ ክልል የሚታየው የፖለቲካ ልዩነት በሰላም እንዲፈታ ምን እየተሰራ ነው? የፕሪቶሪያው ስምምነት ለምን አልተተገበረም?

👉በሀገሪቱ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ይህ ኢትዮጵያ ያለችበትን ለውጥ ያመለክታል፥

👉በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎች በሽፍቶች፤በጽንፈኞች ይገደላሉ፤ይታገታሉ፤ይዘረፋሉና መፍትሄ ቢሰጥ፣

👉መንግስት ጨካ ገብተው ህዝብን ለችግር ከሚዳርጉ ሃይሎች ጋር ልዩነቶችን በሰላም ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል?

👉መንግስት በነዳጅ ላይ ድጎማ ቢያደርግም በአንዳንድ ክልሎች የነዳጅ ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።ይህም በህገወጦች እጅ በመግባቱ እንደሆነ ህብረተሰቡ ቅሬታውን ያነሳል።ቁጥጥሩን ለማጠናከር መንግስት ምን እየሰራ ነው?

👉 በሀገሪቱ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሸማቹን የመግዛት አቅም እየተፈታተነ ይገኛል

👉መንግስት ለግብርናው ዘርፍ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ተጨባጭ የሆነ መልኩ ምርታማነትን አሳድጓል የሚሉት ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም