ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በኢንቨስትመንት ዙሪያ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):-ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በኢንቨስትመንት ዙሪያ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር ) ከሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አምባሳደር ሳከር አል ኩራሺ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በልማትና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ማዕከል ያደረገ ነው።

በተጨማሪም አምባሳደሮቹ በሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ማዕከላት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የመመለሱ ሂደት በትብብር መንፈስ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሙክታር ሙያተኛቾች እና ከፊል ሙያተኞች ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲመጡ የሚያስችለው ስምምነት እንዲፈረም መጠየቃቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም