የጅቡቲ መንግስት ለኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት የመስሪያ ቦታ ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የጅቡቲ መንግስት ለኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት የመስሪያ ቦታ ሰጠ
አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2017 (ኢዜአ):-የጅቡቲ መንግስት በሀገሪቷ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት መስሪያ የአራት ሄክታር መሬት በስጦታ አበርክቷል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፥ የመሬት ስጦታው ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ያላቸው መልካም ወዳጅነት ማሳያ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በመስሪያ ቦታው ላይ በቅድሚያ የመዋለ−ህጻናት ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የገቢ ማሰባሰብ እና በስራ ሂደቱ ላይ ከኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።