ቀጥታ፡

አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን ከሚኖሩ ዳያስፖራዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ)፦ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በሀገሪቷ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት የፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ውሳኔዎች እና ቀጣይ የትኩረት መስኮች አስመልክቶ ለዳያስፖራዎቹ በኤምባሲው በኩል ገለጻ ተደርጓል።

ብሄራዊ አሰባሳቢ ትርክት፣ የሀገር ግንባታ ስትራቴጂዎች፣ ዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አጀንዳዎች እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አቅጣጫዎች ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ ለፖሊሲዊቹ ትግበራ ውጤታማነት ይበጃሉ ያሏቸውን ሀሳቦች ማንሳታቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ኤምባሲው እና ዳያስፖራው የፖሊሲ ትልሞቹ እንዲሳኩ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም