ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የሞሪታኒያ አምባሳደር አሰናበቱ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የሞሪታኒያ አምባሳደር አሰናበቱ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፦ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የሞሪታኒያ አምባሳደር ከድጃ ምባረክን አሰናብተዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አምባሳደሯ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የኢትዮጵያና ሞሪታኒያን ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ እንዲሠሩ ጠይቀዋል።
አምባሳደር ከድጃ ምባረክ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቆይታቸው የማይረሳና መልካም እንደነበር ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግም የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውን ጠቅሰው፤ ይህንንም የበለጠ ለማጠናከር ሚናቸውን እንደሚወጡ አንስተዋል።
የኢትዮጵያና ሞሪታኒያ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት በባህልና ንግድ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።