ቀጥታ፡

ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

በዓለም ንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ የተደራዳሪ ቡድን በ5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ላይ ቡድን ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ይገኛል።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ተደራዳሪ ቡድኑ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር የሁለትዮሽ የገበያ እድል ድርድርን የተመለከተ ስብሰባ አድርጓል።


 

የአውሮፓ ህብረት ላቀረባቸው ጥያቄዎች ከሃገራችን ዘላቂ ጥቅም አንጻር የተቃኙ ምላሾችን ሰተናል ብለዋል፡፡

በመጪው ረቡዕ ከሚካሄድው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባዎች እንደሚደረጉም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም