የአፋርና የሶማሌ ህዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክር የጋራ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአፋርና የሶማሌ ህዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክር የጋራ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
ሰመራ፤መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፦የአፋርና የሶማሌ ህዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክር እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ዓላማ ያደረገ የጋራ ኢፍጣር መርሃ ግብር በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙሰጠፌ መሐመድ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት እና የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
የኢፍጣር መርሃ ግብሩ የሁለቱ ክልሎችን አብሮነት የሚያጠናክር፤ ወንድማማችነት የሚያጎለብት እና ለዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና ለህዝቦች መቀራረብ ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።