ቀጥታ፡

አህጉራዊ ስምምነቱን ሁሉንም አፍሪካዊ ተጠቃሚ ወደሚያደርግ ተጨባጭ ውጤት መቀየር ይገባል-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 8/2017 (ኢዜአ):-በእጃችን ላይ ያለውን ኃይል በመጠቀም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ሁሉንም አፍሪካዊ ወደሚጠቅም ውጤት መቀየር ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በዚህ ወቅት፥ እጃችን ላይ ያለውን ኃይል በመጠቀም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ሁሉንም አፍሪካዊ ተጠቃሚ ወደሚያደርግ እውነታ መቀየር ይኖርብናል ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ታሪክ የሚመዝነን በተፈራረምናቸው ስምምነቶች ብዛት ሳይሆን ባመጣናቸው እውነተኛ ለውጦች ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም