ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ህገ ወጥ ስደትን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 8/2017 (ኢዜአ ):-በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኢድ ኖህ ሀሰን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ ውይይቱ፥ አሳሰቢነቱ እየጨመረ የመጣውን ህገወጥ ስደት እና እያስከተለ ያለውን የዜጎችን ህልፈት በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ከጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ጋር በመሆን ህገ ወጥ ስደትን መከላከል እና ችግሩን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል ውጤታማ የቅንጅት አሰራሮች መዘርጋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም