ቀጥታ፡

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚዛን አማን ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና ሌሎች የክልልና የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ አመራሮች የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ እና የሚዛን አማን አየር ማረፊያ የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

አመራሮቹ በሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የግብርና ልማት ሥራዎች ማለትም የማር ሳይት፣ የሙዝ ችግኝ፣ የሻይ ቅጠል ምርት፣ የቡና ተክል እና ሌሎችንም ጎብኝተዋል።


 

የሚዛን አማን አየር ማረፊያ የስራ እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ እና በከተማ አስተዳደሩ እና በኮሌጁ እየተሰራ ያለው የዶሮ እርባታ ሼድ ግንባታ ሌላኛው የጉብኝቱ አካል እንደነበር የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክትል።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትንን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ

አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም