ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በወቅቱ እንደገለጹት የረመዳን ወር እርስ በእርስ የምንረዳዳበትና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት ነው።
ይህ አብሮነት እና የእርስ በእርስ መረዳዳት የዘወትር ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የዘንድሮውን ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር በቁርአን ሂፍዝ ውድድር የታጀበ መሆኑ ከወትሮው የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብሩ በድምቀት እንዲከናወን አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብሩ ተሳታፊ የሆኑት አብድረህማን ጣሂርና አሊ ሸምሱ በበኩላቸው፤ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነ ስርዓት እርስ በእርስ የምንረዳዳበትና የምንተዋወቅበት ነው ብለዋል።
በመሆኑም በየአመቱ በጉጉት እንጠብቀዋለን ነው ያሉት።
በተመሳሳይ ዛሬ በተካሄደው ሀገር-አቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ፍጻሜ ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ተበርክቷል።
በዚህም በሁለቱም ጾታዎች አንደኛ ለወጡት የመኪና፣ ሁለተኛ ለወጡት የ5 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም ሶስተኛ ለወጡ የ3 መቶ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።