አገር አቀፍ የቁርአን ሂፍዝ የማጠቃለያ ውድድር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አገር አቀፍ የቁርአን ሂፍዝ የማጠቃለያ ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡-አገር-አቀፍ የቁርአን ሂፍዝ የማጠቃለያ ውድድር "ቁርአን የእውቀትና የሰላም ምንጭ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።
የማጠቃለያ ውድድሩ "ቁርአን የእውቀትና የሰላም ምንጭ" በሚል መሪ ሃሳብ ነው በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ የሚገኘው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በውድድሩ ታድመዋል።
ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡ ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር ሲካሄድ መቆየታቸው ይታወቃል።
ለፍጻሜ ውድድሩ ከሁለቱም ጾታዎች ሦስት ሦስት ተወዳዳሪዎች መለየታቸው ይታወቃል።
በተያያዘም የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም ከሰዓታት በኋላ የሚከናወን ይሆናል።
በዚህ አብሮነትንና አንድነትን በሚያጎላው ታላቅ ሥነ ስርዓት ላይ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ይታደማሉ።