የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ማን ያነሳል? ሊቨርፑል ወይስ ኒውካስትል ዩናይትድ? - ኢዜአ አማርኛ
የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ማን ያነሳል? ሊቨርፑል ወይስ ኒውካስትል ዩናይትድ?
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፦ ሊቨርፑል እና ኒውካስትል ዩናይትድ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ዛሬ የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል።
የፍጻሜው ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ 90 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
ሊቨርፑል 10 ጊዜ የካራባኦ ካፕ ዋንጫን በማንሳት በውድድሩ ታሪክ ለበርካታ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። ቀያዮቹ የአምና የውድድሩ አሸናፊ ነው።
ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪኩ የካራባኦ ካፕ ዋንጫን አንስቶ አያውቅም።
ሊቨርፑል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ በአንጻሩ ኒውካስትል ዩናይትድ የዋንጫ ክብሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጨበጥ የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ታዳሚያኑን ትኩረት ስቧል።
ከእንግሊዝ የንግድ ከተማ ሜልተን ሞብሬይ የተገኙት የ35 ዓመቱ ጆን ብሩክስ ተጠባቂውን የዋንጫ ፍልሚያ በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።
እ.አ.አ በ1960 የተጀመረው የካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ዋንጫ) በእንግሊዝ ከአንጋፋው ኤፍ ካፕ ውጪ የሚደረገው የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።