የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ጉባዔ የኢትዮጵያ መጻዒ ጊዜ ብሩህ መሆኑን መልዕክት ያስተላለፈ ነው - አቶ አደም ፋራህ - ኢዜአ አማርኛ
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ጉባዔ የኢትዮጵያ መጻዒ ጊዜ ብሩህ መሆኑን መልዕክት ያስተላለፈ ነው - አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2017(ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ መጻዒ ጊዜ ብሩህ መሆኑን መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ።
ብልጽግና ፓርቲ ለ5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና ለ2ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የፓርቲው 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የለውጥ ጉዞ ስኬቶች የተገመገሙበት ነው ብለዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች አመርቂ የዕድገት ደረጃ ላይ መሆኗ የተመላከተ መሆኑንም ገልጸዋል።
በምስረታ በዓሉ ለቀጣይ ውጥኖች ስኬት የተለያዩ አቅጣጫዎች የተቀመጡበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ባካሄደው 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች የተቀመጡበት መሆኑን ተናግረዋል።
በጉባኤው የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ልማት በቀጣይነትን የሚያረጋግጡ፣ ማህበራዊ ፍትህን የሚያጠናክሩ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች የተለያዩ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ጠቁመዋል።
በሌላ መልኩም ጠንካራ ፓርቲን በመገንባት፣ የኢትዮጵያ ጥቅም የሚያስከበሩ ስራዎችን በማጠናከር እንዲሁም ፓርቲው የጀመራቸውን ውጤታማ ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የመሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የኑሮ ውድነትን መፍታትን እና በሌሎች ዘርፎች አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ጠቁመዋል።
ጉባኤው የኢትዮጵያ መጻኢ ጊዜ ብሩህ መሆኑን መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑንም ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች መተግበር መጀመሩንም ገልጸዋል።
ጉባኤው ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች ዙሪያ እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አመራሮችና የተለያዩ አካላትን ማወያየቱን ተናግረዋል።
ፓርቲው ላስቀመጣቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በየድርሻው ያሉ አካላት ለተግባራዊነቱ የድርሻቸውን መወጣት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎች ዘርፎችም መተግበር መጀመሩን ጠቁመዋል።
በዚህም አመርቂ ውጤቶች መመዝገብ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ የሰጠውን ዕድል በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ሀገር እና ህዝብን የሚያኮሩ ስራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
በሁሉም ዘርፎች አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።