ቀጥታ፡

የሩዋንዳ መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2017 (ኢዜአ)፦ የሩዋንዳ መከላከያ ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲን ጎብኝቷል።

ልዑኩ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ሲደርስ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዲስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም አቀባበል አድርገዋል።

በተመሳሳይ ልዑኩ በመከላከያ ዩኒቨርስቲም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ መኮንኖች አቀባበል አድርገውለታል።

የየተቋማቱ አመራሮችም ለሩዋንዳ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ ተቋማት ስራ ገለጻ አድርገዋል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሩዋንዳ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲን የተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል ።

የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ እና የመከላከያ ዩኒቨርስቲ የሁለቱን ሃገራት ወዳጅነት የሚያሳዩ ስጦታዎችን ለሩዋንዳ መከላከያ ልዑክ አበርክተዋል።


 

የሩዋንዳ መከላከያ ልዑካን ቡድንም ለሁለቱ የመከላከያ ተቋማት ስጦታ ማበርከቱን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም