ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ከካሜሮን ጋር ታደርጋለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ከካሜሮን ጋር ታደርጋለች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከካሜሮን ጋር ያደርጋል።
የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል።
ሀገራቱ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ያውንዴ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ካሜሮን 5 ለ 2 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
በአሰልጣኝ ራውዳ አሊ የሚመራው ብሄራዊ ቡድን ከመጀመሪያው ጨዋታ መልስ በኋላ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ አድርጓል።
ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ካሜሮንን ከሶስት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርበታል።
ብሄራዊ ቡድኑ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በመጨረሻው ዙር ከዩጋንዳ እና ኬንያ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
ዘጠነኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በሞሮኮ አዘጋጅነት በጥቅምት እና ህዳር ወር 2018 ዓ.ም ይደረጋል።
በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። ከሞሮኮ ውጪ አፍሪካ አራት ሀገራትን የማሳተፍ ኮታ አላት።