ቀጥታ፡

ኢዜአ ለእስልምና እምነት ተከታይ አመራሮችና ሰራተኞች የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ለእስልምና እምነት ተከታይ አመራሮችና ሰራተኞች የኢፍጣር መርሐ-ግብር ዛሬ አካሂዷል።


 

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ተፈራ በቀለ የኢፍጣር መርሐ-ግብሩ አብሮነትንና አንድነትን የሚያጎለብት መሆኑ ተናግረዋል።

የኢፍጣር መርሃግብሩ በሠራተኞች መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።


 

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት ሰራተኞች በበኩላቸው፤ ኢዜአ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ-ግብር መደሰታቸውን ተናግረዋል።

መርሃግብሩ አንድነትን በማጠናከር ጠንካራ የስራ መንፈስን ለማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም