የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለማ ያደቻ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሸኽ አብዱልአዚዝ አብዱል ወሊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሡልጣን አማን ኤባ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለማ ያደቻ፤ የመርሐ ግብሩ ዓማ አብሮነትን ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው አየር መንገዱ የሀገር ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።
አየር መንገዱ ላዘጋጀው የኢፍጣር መርሀ ግብር ምስጋና አቅርበዋል።