ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የፍላጎት መግለጫ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሾፍቱ አቅራቢያ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የፍላጎት መግለጫ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።


 

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዌሚ አዴሲና ለኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል አድርገዋል።

ልዑኩ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ያካተተ ነው።


 

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋል ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም