ቀጥታ፡

የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ እና ልዑካን ቡድናቸው አየር ኃይልን ጎበኙ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ እና ልዑካን ቡድናቸው አየር ኃይልን ጎብኝተዋል።

ኢታማዦር ሹሙና ልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል ። 

የሩዋንዳው መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሙባረክ እና በእርሳቸው የሚመራው ልዑካን ቡድን የአየር ኃይልን የበረራ ትምህርት ቤት እና የአቬዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።



 
የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ለሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ስጦታ አበርክተዋል ።
 
በተመሳሳይ የሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ለኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም