ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባህር ኃይል ትብብር ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባህር ኃይል ትብብር ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ በሩሲያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።
ልዑኩ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል እየተገነቡ ያሉ የባህር ሃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያ እና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ ውይይቱ በስልጠናና አቅም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረና መከላከያ የጀመረውን የባህር ኃይል ግንባታ ለማጠናከር እንደሚያግዝ አመልክተዋል።
በዓለም አቀፍ ውሃ ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተቋሙን ዝግጁነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስችልም ገልጸዋል።
ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳና የሩሲያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ አዲሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ በጋራ ባህር ሃይልን በሚያጠናክሩና ለቀጣይ ትብብሮችን ማመቻቸት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።