ኮሚቴው በጅቡቲ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ የጭነት ሂደት ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
ኮሚቴው በጅቡቲ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ የጭነት ሂደት ጎበኘ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦ የጂቡቲ የማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ በአሮጌ ወደብ ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በመጓጓዝ ላይ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ ጭነት እንቅስቃሴ ተመልክቷል።
ኮሚቴው በቀን በአማካይ እስከ 7000 ሜትሪክ ቶን የዩሪያ ማዳበሪያ የሚጫንበት እና ከ112 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች ማዳበሪያውን ጭነው ከተርሚናሉ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙበትን ሂደት ላይ ምልከታ አድርጓል።
የአፈር ማዳበሪያውን የማጓጓዝ ሂደቱ ዘላቂነት ባለው እንዲቀጥል እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።