ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መጋቢት 20 እና 21 ይካሄዳሉ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር መጋቢት 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። 

በዚሁ መሰረት ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና፣ መቻል ከኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ ከሃዋሳ ከተማ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታቸውን በሃዋሳ ከተማ ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 80 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም