ቀጥታ፡

ኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተከፈተ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 04/2017(ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ የኤግዚቢሽን ማዕከል የተዘጋጀውን የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከፍተዋል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ከሚኒስትሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ፣ የሀገራት አምባሳደሮች፣ የምርትና አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

"የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው 14ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋር ያዘጋጁት ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የሀገር ውስጥን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ዓለም ሀገራት የመጡ አምራች ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።

ዓለም አቀፉ የንግድ ትርዒቱ የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የገበያ ትስስርና የልምድ ልውጥጥ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

በዚህም በሀገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞችና ከውጭ ሀገራት በመጡ የንግድ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶች ቀርበው የአቻ ለአቻ የንግድ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድም እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም