ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

የኢንስቲትዩቱ መቋቋም የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ የተሟላ፣ ግልጽ እና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት ያስችላል ተብሏል።

የሒሳብ ሙያን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚወስድና ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ታሳቢ ያደረገ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የሒሳብ ባለሙያ ማፍራት እንደሚያስችልም ተገልጿል።

ምክር ቤቱ የማቋቋሚያ አዋጁን በዝርዝር በማየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም