ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት3//2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከ8ኛ ወደ 6ኛ አሻሽሏል። ድሬዳዋ ከተማ በ22 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። 

ቀን ላይ በተደረጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ መቻልን 4 ለ 2፣ መቀሌ 70 እንደርታ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

ፕሪሚየር ሊጉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ ከጅቡቲ እና ግብጽ ጋር በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ምክንያት እንደሚቋረጥ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

ሊጉ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ውድድር እንደሚመለስ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም