ቀጥታ፡

የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- የኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትን ጎብኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

በጉብኝታቸውም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የሚገኙ ልዩ ልዩ ቅርሶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

በብሔራዊ ቤተ-መንግሥቱ ውብ ገጽታ እና በውስጡ በሚገኙ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች መደነቃቸውንም ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቀድም ብሎ በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም