ቀጥታ፡

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተገኝተዋል።

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ ነገ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና የኮሚሽነሮች ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ ይገኛሉ።


 

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት መሃመድ አሊ ዩሱፍ ከተሰናባቹ ሙሳ ፋኪ ማሀማት ስልጣን በመረከብ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም