በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በዚሁ ወቅት፤ አራተኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በሳምንት ዘጠኝ በረራዎችን በማድረግ ዜጎችን የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ዜጎቹን የመመለስ ተግባር የመንግሥት የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አካል መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በዛሬው ዕለት 43 ዜጎች ከማይናማር መመለሳቸውም ይታወቃል።