ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።


 

ባንኩ ድጋፉን ያደረገው የረመዳን የጾም ወር በማስመልከት መሆኑን ገልጿል።

ድጋፉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ የስራ ሀላፊዎች አስረክበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም