ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሁለትዮሽ ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ሌተናል ጀኔራል ቾል ቶን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ነቢል ከሚኒስትሩ ጋር የሀገራቱ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በአፐር ናይል ግዛት ባለው ወቅታዊ ሁኔታ መነጋገራቸውንም አመልክተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም