ፓትሪስ ሞትሴፔ የካፍ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
ፓትሪስ ሞትሴፔ የካፍ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 3//2017 (ኢዜአ)፦ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል።
ካፍ 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ በግብጽ ካይሮ አድርጓል።
ጠቅላላ ጉባዔው የ63 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) ካፍን ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲያገለግሉ በድጋሚ መርጧቸዋል።
ሞትሴፔ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ካፍን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ ቆይተዋል።
በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር) እና የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፈዋል።