የአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት፣የገንዘብና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያዘጋጀው 57ኛው አህጉራዊ የኢኮኖሚ ልማት፣የገንዘብና የፕላን ሚኒስተሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ፣፣የመንግስታቱ ድርጅት፣የአፍሪካ ሕብረት፣የአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው ጉባዔ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን፤ አፈጻጸሙን የሚያልቁ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን መቀየስ” የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም