በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ዜጎቹን የመመለስ ተግባር የመንግሥት የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አካል መሆኑን ገልጿል።
ኢትዮጵያውያኑ ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያ ዲፕሎማቶችን በማሰማራት ባደረገው ጥረት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
በተያያዘ መንግሥት ጃፓን በሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
መንግሥት ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወዳልተፈጸመባቸው ሀገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ አሳስቧል።