ቀጥታ፡

የካፍ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በካይሮ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 1/2017 (ኢዜአ)፦  የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ በካይሮ ማድረግ ጀምሯል።

ከዋና ጉባዔው አስቀድሞ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) በተገኙበት የክፍለ አህጉር ማህበራት ስብሰባ ዛሬ ተደርጓል።

ነገ የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ይከናወናል።  ረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ ኢዜአ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሬዝዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት  ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር) እና ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ባሕሩ ጥላሁን በጉባዔው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።

የካፍ 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ላይ መካሄዱን ፌዴሬሽኑ በመረጃው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም