የፊፋ ቴክኒካል ኢንስትራክተሮች ስልጠና ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የፊፋ ቴክኒካል ኢንስትራክተሮች ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 1/2017 (ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ ) የአፍሪካ ቴክኒካል ኢንስትራክተሮች ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባባል ስልጠናው በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው ከመጋቢት 1 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ለፈረንሳይኛ ተናጋሪ ሀገራት፣ ከመጋቢት 8 እስከ 12 2017 ዓ.ም ደግሞ ለእንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ኢንስትራክተሮች እንደሚሰጥ ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።