ቀጥታ፡

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጸመ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፦በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጽሟል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ስራ አስፈጻሚ አመራሮች ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በተገኙበት የቦንድ ግዢውን አስረክበዋል።


 

ኮሚዩኒቲው ከዚህ ቀደም በአገራችን ለሚደረጉ የተለያዩ የልማት ጥሪዎች እና ማህበራዊ ድጋፎች ህዝቡን በማስተባበር ትልቅ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ዘንድሮም የ2 ነጥብ7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ የቦንድ ግዥ ለአምባሳደሩ በማስረከብ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም