አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፦ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፍሬድሪኮ ላሜጎ ሶአሬስ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
ኮንፌዴሬሽኑ የብራዚል የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋንኛ ተወካይ ነው።
አምባሳደር ልዑልሰገድ በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ብራዚልን የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ አጋርነት ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መደረሱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በተጨማሪም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በትብብር እንደሚሰሩም አመልክተዋል።