ቀጥታ፡

የአፋርና የሶማሌ ክልሎችን ህዝቦች ትስስርና አብሮነት ለማጠናከር ያለመ የኢፍጣር ፕሮግራም በጂግጂጋ ይካሄዳል

ጂግጂጋ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፡- የአፋርና የሶማሌ ክልሎችን ህዝቦች ትስስረና አብሮነት ለማጠናከር ያለመ የኢፍጣር ፕሮግራም በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ይካሄዳል።

የኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጂግጂጋ ገብተዋል።


 

እንግዶቹን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተቀብለዋቸዋል።

በተጨማሪም የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ ኢድሪስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮችም ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ በስፍራው ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም