ቀጥታ፡

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከዶራሌ ሁለገብ ወደብ ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 1/2017 (ኢዜአ)፦በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ ከዶራሌ ሁለገብ ወደብ ስራ አስፈጻሚ ጃማ ኢብራሂም ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የአፈር ማዳባሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ፥ በዶራሌ ሁለገብ ወደብ እየተሰራ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን አፈጻጸም እና ቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ከስራ አስፈጻሚው ጋር ተወያይተዋል።

የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሂደቱ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ ከጂቡቲ የወደብ ቴክኒካል ኮሚቴ ጋር በሚያደርገው ሳምንታዊ መደበኛ ውይይቶች ላይ የሚነሱ ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የዶራሌ ሁለገብ ወደብስራ አስፈጻሚ ጃማ ኢብራሂም በዘንድሮ ዓመት በተጀመረው ኦፕሬሽን አማካኝነት ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ በሰዓቱ ለማድረስ የማሽነሪዎች ጥገና፣ የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍናን ታሳቢ ያደረገ ስራ መከናወኑን መግለጻቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም