ቀጥታ፡

አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ ሆነው ተሰየሙ

ቦረና፤ የካቲት 30/2017(ዜአ)፦ አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ ሆነው በመሰየም ከ71ኛው የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ስልጣናቸውን ተረከቡ።

የገዳ ባሊ (ሥልጣን) ርክክቡ እሴቱን በጠበቀ መልኩ የተካሄደ ሲሆን፤ የ71ኛው ዙር አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ለ72ኛው ዙር አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ሥልጣናቸውን አስረክበዋል።

ከየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች ሲካሄድ የቆየው መርሃ ግብሩ ዛሬ የሥልጣን ርክክቡ ተካሂዷል።

በሥልጣን ርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኬንያ የልዑካን ቡድን ታድመዋል።

አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮም 72ኛው አባ ገዳ በመሆን ለቀጣዩ ስምንት ዓመታት ስልጣናቸውን ተረክበዋል።

አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ 71ኛው አባ ገዳ ሆነው ላለፉት ስምንት ዓመታት ስርዓቱን በመምራት አገልግለዋል።

72ኛው አባ ገዳ ሆነው የተመረጡት አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮም ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የገዳውን ስርዓት በበላይነት ይመሩታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም