ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በካሜሮን ተሸንፋለች

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29 /2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ባደረገው የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በካሜሮን 5 ለ 2 ተሸንፏል።  

የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ ማምሻውን ያውንዴ በሚገኘው ኦሎምቤ ስታዲየም ተደርጓል። 

ኢትዮጵያ የማጣሪያውን የመልስ ጨዋታ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአበበ በቂላ ስታዲየም ታደርጋለች።

ብሄራዊ ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ካሜሮንን በመልስ ጨዋታው ከሶስት እና ከዚያ በላይ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ቡድኑ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በመጨረሻው ዙር ከዩጋንዳ እና ኬንያ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ዘጠነኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በሞሮኮ አዘጋጅነት በጥቅምት እና ህዳር ወር 2018 ዓ.ም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም