ቀጥታ፡

ኢንስቲትዩቱ በ2025 ኢትዮጵያን ቴክ ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በ2025 ኢትዮጵያን ቴክ ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርቧል።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ግንቦት ከ16 እስከ 18/2025 በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው በኢትዮጵያን ቴክ ኤክስፖ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ጋብዟል።

በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘመን የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ደህንነት በዘመናዊ ከተሞች፤ በኳንተም ስሌት፣ ፋይንቴክ ዙሪያ ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ነው ጥሪ ያቀረበው።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ የፕሮፖዛል ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በፈረንጆቹ ሚያዝያ 20 እንዲሁም የውጤት ማሳወቂያ ጊዜ ሚያዝያ 30 ቀን 2025 መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም