ቀጥታ፡

በአፋር ክልል በመካከለኛው እና በታችኛው አዋሽ የሚከናወኑ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ ተደረገ

አዲስ አበባ፤የካቲት 29/2017 (ኢዜአ)፡- በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ(ዶ/ር) የተመራ ቡድን በአፋር ክልል በመካከለኛው እና በታችኛው አዋሽ የሚከናወኑ የ2017 ዓ.ም የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ አድርጓል።

የጎርፍ መከላከል ስራው በዓለም ባንክ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በመካከለኛው እና በታችኛው አዋሽ የሚከናወን መሆኑ ተመላክቷል።

ሚኒስትር ዴኤታው በወቅቱ እንደገለፁት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የቅድመ ጎርፍ መከላከል ስራ ክረምት ከመድረሱ በፊት ለማስጀመር ውይይት ተደርጓል፡፡


 

የባለፈው ክረምት የጎርፍ መከላከል ስራ ሊደርስ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ በእጅጉ መቀነስ የተቻለ መሆኑን የክልሉ መስኖና ተፋሰስ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቅድመ ጎርፍ መከላከል ስራዎችን መጀመር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በጊዜ መጀመር የሚያበረታቱና ክልሉ በጋራ እንደሚሰራ ቢሮው መግለፁን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከማህበረሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎችም ከክልል እስከ ቀበሌ ባሉ አመራሮች ተለይተው ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ምላሽ እንደሚሰጣቸው መግባባት ላይ መደረሱንም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም