ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል።
ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።