የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ70ኛ ዙር እጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ70ኛ ዙር እጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና ወስደው ያጠናቀቁ የ70ኛ ዙር ቃኘው ኮርስ እጩ መኮንኖችን በዲግሪ መርሃ ግብር እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ጄኔራል መኮንኖች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ወታደራዊ አታሼዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።