ቀጥታ፡

ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እድገት የሁሉም ተሳትፎ አስፈላጊ ነው - ካውንስሉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2017(ኢዜአ)፡- ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እድገት የሁሉም ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ-ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ገለጹ፡፡

ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እድገት የሁሉም ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑንም ነው የካውንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ የገለጹት።

የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ.ም "መለኮታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ የፀሎት እና የስብከት መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡

መርሐ-ግብሩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ ማህበር ቅንጅት ነው።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ-ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ለዘላቂ ሰላምና እድገት በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ዝግጅቱ በርካታ ምዕመን በሚገኝበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ገልጸው፤ በመርሃ ግብሩ ላይ ለሀገር ሰላምና አንድነት ጸሎት እንደሚደረግም ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የፀሎት እና የዝማሬ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም