ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ በዳያስፖራ ተሳትፎ ትብብር ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ በዳያስፖራ ተሳትፎ ትብብር ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በኢትዮጵያ የዩጋንዳ አምባሳደር ጆኒ ሙሂንዶ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር ፍጹም፥ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ በዳያስፖራ ተሳትፎ ሀገርን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ልዑኩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ጤና ክብካቤ እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተሰማራባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመጎብኘት ያለውን የዳያስፖራውን አበርክቶ ለመረዳት መቻሉን ተናግረዋል።
መሰል ጉብኝቶች የዳያስፖራ ተሳትፎ የኢኖቬሽን ዘርፍ በማሳደግ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማሻሻል ረገድ ያለውን አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል አምባሳደሩ በመልዕክታቸው።